ይህ የትምህርት ክፍል ልንግድ ይሚውሉ አበቦች እና የጌጣጌጥ ተክሎች ሥራን ያስተዋውቃል። ተሳታፊዎች ስለ ግሪን ሃውስ አስተዳደር ፣ ስርጭት ፣ የአፈር እና ውሃ አያያዝ ፣ የተባይ መቆጣጠሪያ ፣ ድህረ-መኸር አያያዝ እንዲሁም ሰለ አበባ ንግድ እቅድ አነዳደፍ ይማራሉ።
ዋና ዓላማዎች:
- ተስማሚ የአበባ ዝርያዎችን እና የስርጭት ዘዴዎችን ማወቅ።
- የግሪን ሃውስ እና የመስክ አካባቢዎችን ማስተዳደርያ ስልቶችን መገንዘብ።
- ተባዮችን እና በሽታዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት መቆጣጠር እንድሚቻል ማወቅ።
- በመደርደሪያ ወይም በሽያጭ ወቅት ሕይወትን ለማራዘም ከመከር በኋላ አበቦችን አያያዝ ዘዴዎችን መረዳት።
- ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ የግብይት ስልቶችን ማዘጋጀት።